United Amhara Political Wing

የአማራ ዐንድነት ፖለቲካዊ ክንፍ

Founding principles, core beliefs and values

United Amhara Political Wing (UAPW) has a clear and firm stance, emphasizing a political view with an uncompromising and strict stance towards Amhara political ideologies and policies. The stringent commitment to the interests and identity of the Amhara people in Ethiopia is a dedication to advocating for the rights, well-being, and representation of the Amhara community. United Amhara Political Wing (UAPW) core values include unequivocal stands on the following subjects: (ህገመንግስቱ፣ ሀሰተኛ ትርክቱ፣ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ዐምሐራ ማንነትና ብሄርተኝነት፣ ራስን በራስ ማስተዳደር መብት፣ ርስቶቻችን ይታወቃሉ ካቀናነው የኛ ነው፣ ፋኖ መከላከላከያችን ነው)

  • The Constitution: United Amhara Political Wing (UAPW) does not accept or recognize the current constitution of Ethiopia and regional formations in any form or shape and will never accept or recognize the successive governments formed there after under the disguise of this “constitution”. We will write the constitution as we see fit with a better and strong representation of an Amhara party.
  • Historical Narrative: United Amhara Political Wing (UAPW) works diligently by highlighting the historical contributions and achievements of the Amhara people by challenging or revisiting historical narratives that are perceived as neglecting or downplaying the role of the Amharas in Ethiopian history. We strongly denounce and oppose the false narration spread by our adversaries.
  • Historical Adversaries: United Amhara Political Wing (UAPW) is taking a strong and explicit stance against certain organizations and movements, labeling them as anti-Amhara. The mentioned organizations include the Oromo Liberation Front/Army (OLF/OLA/OPDO), Prosperity Party (PP) formerly known as EPRDF, and the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), among others. By expressly rejecting the ideologies of these entities and declaring the Amhara Democratic Party (ADP) which is a part of PP as the “#1 Amhara enemy,” UAPW is taking a clear and unwavering position on its perceived adversaries within the political landscape.
  • Emphasis on Amhara Identity and Amhara Nationalism: The United Amhara Political Wing (UAPW) strongly emphasizes the promotion and preservation of a strong Amhara nationalism, identity, culture, language, and heritage. We believe that safeguarding Amhara identity and traditions is essential for maintaining our independence. UAPW advocates for traditional values, limited government intervention, and a focus on law and order. As the largest ethnic group in Ethiopia, we assert that Amharas should hold the majority of positions within the country’s administrative institutions at a local, regional and federal level. Amhara nationalism takes priority over Ethiopia. Our journey begins with Amhara and is destined to culminate with Amhara, and continuously striving to make Amharas great again.
  • Regional Autonomy: Advocating for increased political and administrative autonomy for the Amhara state where we emphasize our unique role as the primary determinant of the rightful lands or territories of the Amhara people within Ethiopia, and challenging the current “federal?” structure in favor of Amhara interests.
  • Land, Resource Rights and Historical Claims: United Amhara Political Wing (UAPW) prioritizes issues related to land ownership and resource distribution, aiming to secure what we perceive as rightful access and control over these resources for the benefit of the Amhara people by asserting historical claims to certain territories or resources and demanding recognition and redress for perceived historical injustices against the Amhara people.
  • Amhara Defense Force ነፍጠኛ: United Amhara Political wing (UAPW) firmly believes an armed struggle is the only and best option remaining in resolving our issues and repelling the existential threats that have been waged on Amharas by anti-Amhara entities. Amharas have to control all branches of government if this country should continue in its current format, if not, we highly consider establishing an Amhara nation with the borders demarcated in our likings. No negotiation with Oromuma, no peace with Oromuma and no recognition of Oromia. Therefore, UAPW supports FANO forces and believes that the different factions of FANO forces should be united into one force forming Amhara Defense Force (ADF). UAPW stands behind the finalized and released plan to all regional Fano leaderships, which outlines the ADF structure centered only around the greater Shewa (ሸዋ ጠቅላይ ግዛት).
  • ጉዳዩ፦ የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ United Amhara Political Wing (UAPW) መሠረታዊ መርሆዎች፣ ቁልፍ ዕምነቶች እና ዕቶች፡
  • የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ በአማራ የፖለቲካ ሱታፌ ዐውድ የነጠረና የራሱን ዐዕማድ ያዋቀረ ሆኖ፣ በአማራ መጻዒ ዕጣ ላይ ለማናቸውም ድርድር የማይቀርብ ርዕዮት እና ፖሊሲዎች አሉት። በብቸኝነትም የአማራ ነገድ (ማኅበረሰብ) ፍላጎትና ማንነት ማጠየቂያ ማንጸሪያ ተቋም ሲሆን፣ የአማራን ሁሉን-አቀፍ ፖለቲካዊ ውክልና፣ የጸና ደህንነት እና የማይገሰሱ መብቶች ባለቤት በማድረግ ሂደት ውስጥ የማይናወጥ አቋም አለው። የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ በጽናት የሚቆምላቸው ቁልፍ ዕሴቶቹም ሕገ-መንግስቱን በመለወጥ፣ ሐሳዊ ትርክትን በመርታት፣ ታሪካዊ ባላንጣዎችን ከማክሰም፣ የአማራ ማንነትና ብሔርተኝነትን በጽኑ መሠረት ስለማኖር፣ አማራዊ የአገረ-መንግሥት ባለሟልነትን ማስቀጠል፣ ዐጽመ-ርስቶቻችን ደጃፎቻቸውን ማስከበር እና ፋኖ የአማራ መከላከያ መሆኑን በስፋት ማሳወቅ ነው።
  • ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳይ፡ የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እና የክልሎች አመሠራረት፣ አወቃቀርና ሕገ-መንግሥቱ ያደራጀውን የጎሳ ሥሪት በፍጹም አይቀበልም፣ ዕውቅናም አይሰጥም። የአማራ ሕዝብና ፖለቲካዊ ርዕዮት ሱታፌ የተረጋገጠበት የአማራን ሁለንተናዊ ጥቅሞችን የሚጠብቅና የሚያረጋግጥ አዲስ ሕገ-መንግሥት እናዘጋጃለን፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥሪትም እናጸናለን።
  • ሐሳዊ ትርክት፡ የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ አማራ በኢትዮጵያ ግዛተ-መንግሥት እና ታሪክ ውስጥ አንኳር ድርሻ ማበርከቱን በሸፍጥ በማኮሰስና በሐሳዊ ትርክት በመተካት ሲሳደድና ሲባዝን እንዲኖር ተደርጓል። ይህን የተንሻፈፈ አውዳሚ ትርክት በማክሰም በኢትዮጵያ የታሪክና ሥልጣኔ ማዕድ ተገቢውን ክብርና ተግባራዊ ትሩፋት እንዲጎናጸፍ አድርገን ዳግም እንተክላቸዋለን። በታሪካዊ ሻጥረኞች የተካበውን ሐሳዊ ትርክት ከመቃወም አልፈን የጥላቻ ካምፑን እናፈርሳለን።
  • ታሪካዊ ባላንጣዎቻችንን ማክሰም፡ የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ አማራን በጠላትነት፣ በጨቋኝነትና በፊውዳልነት የሚያሳድዱትን ዐጽራረ-አማራ ስብስብ፣ አደረጃጀቶችና ማናቸውንም ንቅናቄዎች እስከ አስተሳሰባቸው እስከፍጻሜው ይፋለማል። ከሚፋለማቸው ዕልፍ ዐጽራራት ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ሠራዊት ወይም በእንግሊዝኛው ምኅጻረ ቃል (OLF/OLA/OPDO)፣ ቀድሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ይባል የነበረው ተገጽላ የብልጽግና ፓርቲ (PP)፣ እና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አቅጪ ግንባር (ሕወሐት/TPLF) በጥቂቱ ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ የተሳከረ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ የጥፋት ችቦ ተሸካሚውን ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን/ADP) ኋላም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሲባል ቆይቶ አሁን የብልጽግና ክንፍ በሆነው ስብስብ ላይ “የአማራው ጠላት” ስለመሆኑ ጽኑ አቋም አለን።
  • የአማራ ማንነትና ብሔረተኝነት፡ የአማራን ብሄርተኝነት፣ ማንነት፣ ባሕል፣ ቋንቋ፣ ቅርስና ትውፊት በማሳደግና በማስፋፋት ለሕልውናው የሚገዳደሩትን ኃይላት በማሸነፍ በትዕምርታዊ ጎዳና እንጓዛለን። የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ ነባር ገዢ ዕሴቶችን ያበረታታል፣ የመንግሥትን ጠቅላይነትና ጣልቃ-ገብነትን የሚገድብና በሕግና ሥርዓት የሚመራ እንዲሆን ይሠራል። ፖለቲካዊ ክንፉ አማራ በባሕል፣ በታሪክ ይዞታውና በሕዝብ ቁጥሩ ግዙፉ እንደመሆኑ በአገሩ ፖለቲካዊና የፍትሕ ተቋማት ውስጥ ተገቢውን እና ትልቁን ሥፍራ ዕንዲይዝ አጥብቆ ይሠራል።  እራሱን ከመጥፋት ለመከላከል የሚሠራው የአማራ ብሔረተኝነት ከኢትዮጵያ ማዕቀፍ ቀዳማይ ውጥን ሆኖ ይቀጥላል። ፖለቲካዊ ማጠንጠኛችን እና ጉዟችን በአማራነት ጀምሮ በአማራነት ይደመደማል።
  • ራስ-ገዝነት፡ የፌደራል መንግስት አግላይ ዕሳቤዎችን በማፍረስ፣ በጊዜና ቦታ ጥልቀት ውስጥ ዘልቆ ለትውልዱ ያወረሰውን የአማራ መንግስታዊ ትልሞችና ዕሴቶች በማሳደግ፣ ግዛታዊ አንድነቱን እና ራስ-ገዝ ሚናውን በማላቅ፣ የአማራን ፖለቲካ-ኤኮኖሚ መሪነት ገዢ ትርክት በማድረግ አማራዊ የአገረ-መንግሥት ባለሟልነትን ማስቀጠል ቀዳሚ ግባችን ነው።
  • ዐጽመ-ርስቶቻችንን ማጽናት፡ በታሪክ፣ በባሕል እና መልክዐ-ምድራዊ ሥሪታቸው የአማራ የሆኑ ግዛቶች የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ ቋሚ ግብ ናቸው። እነዚህንም ርስቶች፣ በውስጣቸው የያዟቸው ሐብቶችና ጸጋዎች ፍትሐዊ የአማራ ቋሚ ትሩፋቶችና የነገ መንገዱ ፍኖት ማቅኛ መሆናቸውን በአጽንዖት እንይዛለን። በታሪክም ከነዚህ ጸጋዎቹ እንዲርቅ፣ እንዲባዝን እና እንዲታረዝ ያደረጉ ትርክቶችንም በማክሰም ይጓዛል።
  • ነፍጠኛ -የአማራ መከላከያ ዘብ፡ የተደራጀ የትጥቅ ትግል ብቸኛው የአማራ የመጥፋት አደጋ መቀልበሻ እና የታወጀበትን የዘር ማጽዳት ጦርነት የማርከሻ መንገድ እንደሆነ የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ ያምናል። አማራ በኢትዮጵያ አገረ-መንግስት ቁልፍ የመንግስት ማለትም የሕግ ማውጣት፣ አስፈጻሚውን እና የፍትሕና የብሔራዊ ደህንነት ተቋማት ላይ ንዑድ ድርሻ መያዝ አለበት። ይሕ ካልሆነ በአባቶቹ ፍኖትና አገረ-ሰሪነት ጥበብ ተመርቶ በፈቀደውና የእኔ በሚለው ታሪካዊ ግዛቱ የራሱን መንግሥት ይመሠርታል። ከኦሮሙማ ዘር አጥፊ አገዛዝጋር በፍፁም አይደራደርም፣ለኦሮሙማ ሥርዓት አይገዛም፣ ኦሮሙማ ጋር የሚጋራው ቁራሽ ማዕድ አይኖርም፣ የኦሮሚያን ክልልና ለኦሮሙማ ዝንተ-ዓለም ዕውቅና አይሰጥም። በመሆኑም የአማራ ዐንድነት (ዐዕማደ አማራ) ፖለቲካዊ ክንፍ የፋኖን ትግል እና አደረጃጀት በሙሉ ዕምነት ይደግፋል፣ የተለያዩ የአማራ ፋኖ ቡድኖች በአንድ ዐሐድነት አድገው የመናገሻ አቅሪያቢያ የሆነውን ሸዋ ጠቅላይ ግዛትን ማእከላዊ ባደረገ አካሄድ የአማራ መከላከያ ዘብ (Amhara Defense Force – ADF) እንዲመሠረት አበክሮም ይሠራል። 

    ማዕከላዊ ኮሚቴ
    የአማራ ዐንድነት ፖለቲካዊ ክንፍ
    ድል ለፋኖ!
    ድል ለአማራ!
Victory to Fano‼️
Victory to Amhara‼️